አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ 19ኛውን ዓለም አቀፍ የቲቢ ምርምር ኮንፍረንስና የዓለም የቲቢ ቀንን እንዲያዘጋጁ ተመርጠዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ታኅሣሥ 18/2017 ዓ/ም የምርምር ኮንፍረንሱ ዋና አዘጋጅ ኮሚቴ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና መርሃ ግብሩን ለማስፈጸም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ እና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ተወጣጥተው ከተደራጁ የኮሚቴ አባላት ጋር ስለ ኮንፍረንሱ ዓላማ፣ በሚኖሩ መርሃ ግብሮችና በተቋማት የሥራ ድርሻ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት የበኩላቸውን ለመወጣት ከአሁኑ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎችን ለመጀመርና በትብብር ለመሥራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

ከመጋቢት 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው መርሃ ግብር ላይ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት የተወጣጡ በርካታ ተሳታፊዎች የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ የምርምር ሥራዎች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት