የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2009 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ Click here to download the full information.
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
- የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና 3 ፎቶ ኮፒ እንዲሁም 3 ጉርድ ፎቶ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/ Official Transcript/
- የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ 3 ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter
- የመመዝገቢያ ክፍያ፡- 40 ብር እና የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 211 እና ከዩቪርሲቲው ዌብሳይት (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግል አመልካቾች፡- ከሚሰሩበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በመንግስት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsorship Form / ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 211 እና ከዩቪርሲቲው ዌብሳይት (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማመልከቻ' የፈተና መስጫ 'የውጤት ማሳወቂያ' የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
- የማመልከቻ ጊዜ ፡- ከነሐሴ 15/2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2008 ዓ.ም
- የማመልከቻ ቦታ ፡-አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቅበላ ክፍል 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት/አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን /
- የመግቢያ ፈተና፡- መስከረም 13 /2009 ዓ.ም ለፈተና ያለፉ የሚገለጽበት ሲሆን መስከረም 18/2008 ዓ.ም በድህረ ምረቃ ት/ቤት ፈተና ይሰጣል
- የምዝገባ ጊዜ ፡- መስከረም 19-20 /2ዐዐ9 ዓ.ም
- ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ፡- ጥቅምት 1/2009 ዓ.ም
ማሳሰብያ፡- ማንኛውም አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/ Official Transcript/ በምዝገባ ወቅት ካላቀረበ መመዝገብ አይችልም፡፡
አርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አሉሙናይ ዳይረክቶሬት ጽ/ቤት