የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጥር 24/2017 ዓ/ም በተካሄደው የሴቶች የቼዝ ፍጻሜ ውድድር በሳምራዊት ግርማ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ አግኝቷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ተማሪ ሳምራዊት በውድድሩ አንድም ሽንፈት ያላስተናገደች ሲሆን ከተካሄዱ 7 ዙሮች 6ቱን በመርታት በአንዱ አቻ በመለያየት በአጠቃላይ 6.5/7 ነጥብ በማምጣት የወርቅ ሜዳልያ ለዩኒቨርሲቲው አስገኝታለች።
የቼዝ አሠልጣኝ መ/ር ጌታሁን ሞኝነት በውጤቱ ደስተኛ እንደሆነና የተመዘገበው ስኬት በሌሎችም የስፖርት ዓይነቶች መሰል ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ እንዳለው በመጠቆም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፏል ።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት