አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ ምርምርና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት የካቲት 26/2017 / ተፈራርመዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በስምምነት ሰነዱ ላይ እንደተመላከተው ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህራንና ተማሪ ልውውጥ፣ የቤተ-ሙከራ ግብአቶችን በጋራ መጠቀም፣ በሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅት፣ የምርምር ኮንፈረንሶችን በጋራ ማዘጋጀት፣ ፈንድ በማፈላለግ፣ የጋራ የምርምር ፕሮጀክቶችና ቀርጾ በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ ዓመት በኋላ ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በርካታ ጠንካራ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረው ዩኒቨርሲቲው በተለይ በምኅንድስናው ዘርፍ ምሁራንን ከማፍራት ባሻገር ሀገርንና መንግሥትን የኃይልና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን በመሥራትና በማማከር የማገዝ ውጥን እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመሥራት መስማማታችን ያለንን የሰው ኃብትና ሌሎች ግብአቶች በጋራ ለመጠቀም የሚያግዝ ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ ትብብሩ ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመሥራት የሚረዳ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ዩኒቨርሲቲው ቁርጠኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከማንዳንት /ጄነራል ከበደ ረጋሣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከነበረበት ጊዜ አንስቶ የሚያውቁት መሆኑን ተናግረው ተቋሙ በውኃ ምኅንድስናና በሌሎች ዘርፎች በርካታ ምሁራንን ማፍራት የቻለ የሀገር ባለውለታ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲያቸው ለመከላከያ ልኅቀት የሚሰራ መሆኑን ያወሱት /ጄኔራሉ ለዚሁ ዓለማ የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነቱ ማስፈለጉን አብራርተዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች /ፕሬዝደንት / / ቦጋለ /ማርያም ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጋር ኮሌጅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ  ግንኙነት የነበረ መሆኑን አስታውሰው እንደ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማሩ ዘርፍ በስምምነት ሰነዱ መሠረት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ሁሉ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኝነት መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

የምርምርና ትብብር /ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ በበኩላቸው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በምርምሩ መስክ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የተለያዩ የምርምር ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በትብብር የመሥራት የካበተ ውጤታማ ልምድ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በእንሰት፣ በታዳሽ ኃይል፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በጤናና በማዕድን ዘርፍ የሚደረጉ የምርምር ሥራዎችን ለአብነት የጠቀሱት / ተክሉ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተለያዩ ለሀገር ጠቃሚ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የትብብር የምርምርና ፈጠራ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ለመሥራት ዝግጁነት መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ መካላከያ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ኮማንዳንት / ተስፋዬ ቶሎ ዩኒቨርሲቲው በጤና፣ በምኅንድስናና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች ለመከላከያው የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ላይ እንደሚሰራ ገልጸው በተለይ በሚሊተሪ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራችን ራሷን እንድትችል የማድረግ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ተግባራትን ለመፈጸም እንደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካሉ አንጋፋ ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን ያወሱት / ተስፋዬ በተለይ በምግብ፣ በሜካኒካልና ኤልትሪካል ምኅንድስና፣  በቴክኖሎጂ፣ በባዮ ቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን አብራርተዋል፡፡

ከስምምነቱ ባሻገር በዕለቱ ከኢትዮጵያ መካላከያ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ከፍተኛ አመራር አካላት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን እንዲሁም በዓባያና ዋናው ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ቤተ መከራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

 

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /