በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የማሪታይም ምኅንድስና ትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናና ገለጻ ከማሪታይም ባለሥልጣን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የካቲት 28/2017 / ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

''Introduction to Maritime Laws on Marine Education" "Regulatory Compliance and Accreditation" Curriculum Development" "Infrastructure and Resource"  " Faculty and Instructors" Industry Partnership" እና " Financial and Administrative Planning" የሚሉት ገለጻው የተሰጠባቸው ርእሰ ጉዳዮች ናቸው።

የአካዳሚክ ጉዳዮች /ፕሬዝደንት / / ቦጋለ /ማርያም  ምኅንድስና ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል ዋነኛው እንደመሆኑ በማሪታይም ምኅንድስና ፕሮግራም ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል። ከማሪታይም ባለሥልጣን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የዘርፉን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያስረዳ ሙያዊ ሥልጠናና ገለጻ መሰጠቱ በዓለም አቀፍ ገበያ ጥራት ያላቸው ምሩቃንን ማፍራት የሚያስችል ሥርዓተ ትምህርት ለመቅርጽ እንዲሁም አስፈላጊውን ግብአትና ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር  / ሙሉነህ ለማ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ 2014 / ጀምሮ በማሪታይም ምኅንድስና የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ፕሮግራሙን ለመክፈት ኢንስቲትዩቱ ከማሪታይም ባለሥልጣን ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝና ለፕሮግራሙ መማር ማስተማር አገልግሎት የሚውል በአባያና ጫሞ ሐይቆች ዳርቻ የመሬት መረጣ የተደረገ መሆኑንም / ሙሉነህ ገልጸዋል፡፡ የማሪታይም ባለሥልጣን ፕሮግራሙ እንዲከፈት ከፍተኛ ጥረትና ድጋፍ በማድረግ ወደ ተለያዩ ተቋማት በመውሰድ ተሞክሮ እንድናገኝ ያደረጉት ተነሳሽነት የሚመሰገን ነው ያሉት / ሙሉነህ በተጨማሪም የማሪታይም ባለሙያዎች ከፕሮግራሙ ጋር ያለውን ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁኔታና ተሞክሮ ማካፈላቸው ፕሮግራሙን በፍጥነት ለመክፈት በእጅጉ የሚረዳ እንደሆነም አውስተዋል።

የማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ካፒቴን ክብሩ መስፍን ከማሪታይም እንደስትሪ ጋር ተያይዞ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን በገለጻቸው የዳሰሱ ሲሆን በዘርፉ የሚሰጥ ሥልጠና በከፍተኛ ደረጃ ጥራቱን የጠበቀ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡  ከማሪታይም ሥልጠና ጋር በተገናኘ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው  እንደ ሀገር  በሚቀጥሉት  አምስት ዓመታት በመስኩ ሰባ ሺህ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በማሪታይም ባለሥልጣን ሲኒየር ማሪን ሰርቨየርና ኤግዛማይነር ቺፍ / ሸዋንግዛው ካሳ ማሪታይም ትልቅ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸው በዘርፉ ሠልጥነው የሚመረቁ  ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ገበያ ጭምር የሚፈለጉ ናቸው ብለዋል።  አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዙሪያው ሁለት ሐይቆች በቅርበት  ያለበት አካባቢ መሆኑ  ፕሮግራሙን ለማስጀመርና ጥራት ያለው ሥልጠና ለመስጠት ሞቹ ያደርገዋል ያሉት ኢንጂነሩ ይህም ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በዘርፉ ለሀገርና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች የቀረበውን ገለጻ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ የተሰጣቸው ሲሆን በመርሃ ግብሩ የቴክኖሎጂና የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች የሥራ ኃላፊዎችና መምህራን እንዲሁም ሌሎች የዩኒቨሲቲው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት