በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮምፕዩቲንግና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋካልቲ አዘጋጅነት ˝Artificial Intelligence for Academic Research: Supercharge your Workflow˝ በሚል ርእስ የዘርፉ መምህራንና ተመራማሪዎች በተገኙበት የካቲት 28/2017 ዓ.ም ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
‹‹Introduction to AI››፣ ‹‹Literature Review and Enhancing Writing with AI››፣ ‹‹Research Intelligence Solutions and Ethical Use of AI›› የሚሉት በወርክሾፑ ከተዳሰሱና ገለጻ ከቀረበባቸው ርእሰ ጉዳዮች መካከል ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የትምህርት ዘርፉን የሚነካ ዘመኑ የወለደው ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልጸው ቴክኖሎጂው ሰዎችን ባይተካም የሰዎችን ሥራ ለማቀላጠፍና ለማቅለል ይረዳል ብለዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ሙሉነህ ወርክሾፑ ቴክኖሎጂው ጠቀሜታው የጎላ ቢሆንም በአግባቡ ካልተመራና ካልተያዘ አሉታዊ ተጸዕኖ እንደሚኖረው የሚያስገነዝብ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የኮምፕዩቲንግና ሶፍተዌር ምኅንድስና ፋካልቲ ዲንና የወርክሾፑ አስተባባሪ አቶ ጌታሁን ትግዕስቱ በአሁኑ ወቅት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በተያያዘ አዳዲስ እየበለጸጉ ያሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት እየታዩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እንደ አካዳሚክና ምርምር ተቋም የትኞቹን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ብንጠቀማቸው ውጤታማ መሆን እንችላለን በሚሉት ነጥቦች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡
በወርክሾፑ ከሁሉም ካምፓሶች የመጡ መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ የ2ኛና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት