አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከአይስ-አዲስ (ice-Addis) ጋር በመተባበር በኢንተርፕርነሪያል ጽንስ ሃሳብ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ዲጂታል ፕላትፎርሞችን መጠቀም ዙሪያ ተሞክሮን የማጋራትና ግንዛቤን መፍጠር የሚያስችል መድረክ መጋቢት 19/2017 . ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ገንዘብን ለመስራት የሚያግዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለሚያመጡ  ሥራ መጀመር የሚያስችላቸው መነሻ ገንዘብ ማፈላለግና የሥራ ዕድል ማመቻቸት፣  የግብይት ትስስር እንዲፈጠሩ የሚያስችል ግንዛቤን መፍጠር፣ ፅናትና ትግዕስትን በመላበስ እስከ መጨረሻው ፈተናን በመጋፈጥ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል የሚያሳዩ የሕይወት ተሞክሮዎች፣ « E-Learning»እና« E-commerce» ዙሪያ አቅምን መገንባት እንዲሁም በገበያው ተወዳዳሪ የሚሆኑ ስታርታፖችን መፍጠርና ማነቃቃት በዕለቱ ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡

የሥራ ፈጠራና ሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክተር / ወንድወሰን ጀረኔ ዳይሬክቶሬታቸው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሰሩ የምርምር ውጤቶች ለገበያ እንዲበቁና ለማኅበረሰቡ መሸጋገር እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን ገልጸው በተለይ የቢዝነስ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወጣቶች በእጃቸው በያዙት ስልክ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ሥራ ፈጥረው ገንዘብ ማግኘትና ሕይወታቸውን መቀየር እንደሚችሉም / ወንድወሰን አንስተዋል፡፡

«ice-addis»ፕሮጀክት ማነጄርና የቨንቸር 360 አስተባባሪ አቶ በረከት ያዕቆብ የተለያዩ ማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ገነዘብ መሥራት እንደሚቻል አውስተው በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ሥራ ፈጣሪዎች የቢዝነስ ሃሳባቸውን በቀላሉ ለማ ኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቴሌግራምን ስለሚጠቀሙ  የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶችም በመረጡት ፕላትፎርም በመጠቀም የቢዝነስ ሃሳባቸውን ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡ ድርጅታቸው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 8  ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወጣቶች «E-Commerce»እና «E-Learning» ግንዛቤ  አግኝተው የተለያዩ  ስታርታፖችን መፍጠር እንድችሉ እንደሚያግዝና እንደሚያበረታታ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከአርባ ምንጭ ተነስቶ አሜሪካንን ጨምሮ በተለያዩ ውጭ ሀገራት ጃኖ ሸማ በሚል የባሕል አልባሳት ላይ ብራንዱን በማስተዋወቅና በማቅረብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ወጣት ሥራ ፈጣሪ  ፍሬው ቆንጆ   በክብር እንግድነት ተጋብዞ የሕይወት ተሞክሮውንና ልምዱን አጋርቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና  የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ /ቤት 11 እና 12 ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ከተማ የተወጣጡ  ወጣቶች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት