የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዩች አካቶ ትግበራ /ቤት በጫሞ ካምፓስ ለሚገኙ ዐይነ ስውር ተማሪዎች ከየካቲት 29/2017 . ጀምሮ ለአራት ቀናት የቆየ መሠረታዊ የኮምፕዩተር ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዩች አካቶ ትግበራ /ቤት ሥራ አስፈጻሚ /ሪት ሠናይት ሳህሌ ሥልጠናው 0ይነ ስውራን ተማሪዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችሎታቸውን በማሻሻል በትምህርታቸው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ዓላማ በማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

በቦንጋ ዩነቨርስቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ትምህርት ክፍል መምህርና አሰልጣኝ  ታደለ ታፈሰ  ዐይነ ስውራን ተማሪዎች ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ እና የሚሰጣቸውን የትምህርት ኮርሶች በቀላሉ መማር እንዲችሉ ሥልጠናው የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ጉዳዩች አካቶ ትግበራ ባለሙያ / ዳግማዊት አባይነህ ዐይነ ስውራን ተማሪዎች በሥልጠናው ያገኙትን የቴክኖሎጅ ዕውቀት ለመጠቀም ወደ ተግባር ለመቀየር የበኩላቸውን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡       

የአካል ጉዳተኞች ተማሪዎች  ተወካይ  የሆነው ተማሪ ሰኝ  ሁንዴ ሥልጠናው ከኮምፕዩተር አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑንና በዩኒቨርሲቲው መሰል ሥልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ገልጿል፡፡

ሥልጠናው በሶፍት ዌርና በኢ-ሜይል አጠቃቀም እንዲሁም በፓወር ፖይንት አዘገጃጀት እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ያተኮረ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት