የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለሳይንስ ትምህርት ጥራት መሻሻል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን / ቴዎድሮስ ብርሃኑ ለሳይንስ ትምህር ጥራት መሻሻል ቁልፍ ተግባራትን በመለየት የሳይንስ ትምህርት /ራንን አቅም በማጎልበትና የሰው ኃይል በማልማት፣ መሠረተ ልማት በማስፋፋት እንዲሁም በግብአት የተሟላ የምርምር ቤተ-ሙከራ በማደራጀት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለሳይንስ ትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ማጠናከሪያ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማስተዋወቅ በርካታ ማኅበረሰብ ተኮር ተግባራት መከናወናቸውን አክለዋል፡፡

ለሳይንስ ትምህርት ጥራት መሻሻል በታችኛው የትምህርት ደረጃ ሕጻናት ሳይንስን ወደውትና ፈልገውት እንዲማሩት ማድረግ፣ በቤተ-ሙከራ የተደገፈ ተግባር ተኮር የትምህርት ሥርዓት መፍጠር እንዲሁም ለሳይንስ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ መሆኑንም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ማስተባበሪያ /ቤት አስተባባሪ / ተስፋዬ /ማርያም ለሳይንስ ትምህርት ጥራት መሻሻል ኮሌጁ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው በዚህም የኮሌጁ መምህራን  በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኮሚዩኒቲ፣ ልማት እንዲሁም በጫሞ 2 ደረጃ /ቤቶች 9-12 ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር የሳይንስ ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ኬሚካሎችን በማስወገድ ረገድም ኮሌጁ  750 ሺህ ብር ፕሮጀክት በመቅረጽ በጋሞ  ዞን በሚገኙ አሥር  2 ደረጃ  /ቤቶች ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩና የተከማቹ የተለያዩ ኬሚካሎችን ጤናማነት የመለየት፣ የማደራጀት እንዲሁም ለሳይንስ ትምህርት /ራን ሥልጠና በመስጠት ቤተ-ሙከራዎቹ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሰፊ ሥራ መሰራቱን / ተስፋዬ አክለዋል፡፡

በኮሌጁ የሚገኙ የሳይንስ ትምህርት ቤተ-ሙከራዎች ሀገር አቀፍና  ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም ኮሌጁ ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት