የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በዋናው ግቢ ያስገነባውን የሕጻናት ማቆያ ማዕከል ሥራ ለማስጀመር የማዕከሉን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት አስመልክቶ ሚያዝያ 7/2017 ለህጻናት ወላጆች ገለጻ (Orientation) ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
በዕለቱ የማዕከሉን የአሠራር ሥርዓት እና የወላጆች መብትና ግዴታን የያዘ ሰነድ ውል ከወላጆች ጋር ተገብቷል።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዩች አካቶ ትግበራ ቡድን መሪ አቶ አብዩት በላይነህ ማዕከሉ ሰባት የሕጻናት ተንከባካቢዎችና ሁለት የፅዳት ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ተናግረዋል። ማዕከሉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው በኮሚቴ የተመለመሉ ሃያ ስድስት ሕጻናትን ይዞ ሥራ የሚጀምር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት