የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ- ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪ የሆነው ናትናኤል ፀጉ አሰፋ ከጓደኛው ጋር በተፈጠረ የግል ፀብ በደረሰበት ጥቃት ዛሬ ጠዋት ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ/ም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል:: በመሆኑም ሕይወቱን ለማትረፍ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግም ሳይሳካ በመቅረቱ ማምሻውን 12:30 ላይ ሕይወቱ አልፏል።
ጥቃቱን ያደረሰው ተማሪ በቁጥጥር ስር ውሎ አስፈላጊው ምርመራ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የሕግ ሂደቱን በመከታተል ውሳኔውን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል::
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ናትናኤል ከዚህ አለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት