የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ በዚህ ሀገራዊ መርሐ ግብር ላይ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ እያሳሰብን በዕለቱ የሚኖረው መርሐ ግብር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1.የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላትና ከፍተኛ አመራሮች በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ የችግኝ ተከላውን የሚያከናውኑ ይሁናል፡፡

2.መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በየካምፓሱ ለተከላው በተዘጋጁ ቦታዎች የችግኝ ተከላውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ለሚካሄደው የተከላ መርሐ ግብር ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን የትራንስፖርት አገልግሎት ያዘጋጃል:: በየካምፓሶች የሚደረገውን የችግኝ ተካላ መርሐ ግብር የካምፓስ ኃላፊዎችና የማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የሚያስተባብሩ ሲሆን ከነገ ሐምሌ 23/2017 ዓ/ም ጠዋት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ችግኝ ጣቢያ በመገኘት በየካምፓሶቻችሁ ለሚኖረው የተከላ መርሐ ግብር ችግኞችን እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡