የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲው ሲኒየር መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በግርጫ የደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር ማዕከል  የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዛሬ ነሐሴ 24/2017 . አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

መርሐ ግብሩ ከችግኝ ተከላ ባሻገር ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች የምርምር ማዕከሉን አቅምና ነባራዊ ሁኔታ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ ነው።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል የዕለቱ መርሐ ግብር ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ተመራማሪዎች የምርምር ማዕከሉ ያለዉን ትልቅ አቅም ለማስተዋወቅ የታሰበ መሆኑን በመግለፅ ተመራማሪዎች  በምርምር ማዕከሉ ያለውን ሰፊ ሀብት በመጠቀም የምርምር ስራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር /ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ የምርምር ማዕከሉ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በሳይንስ፣  በፈጠራና በግብርና ምርትና  ምርታማነት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡   በማዕከሉ  ከደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር በተጨማሪ የወትት ምርትና ምርታማነትን ለማሳድግ የምርምር ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንና ለማኅበረሰቡ እንደምሳሌ ሊሆን የሚችል ሳይንሳዊ መንደር እየተገነባ እንዳለ ተናግረው በቅርቡም ከዓለም ደን ተቋም ጋር በመተባበር  በሀገር ውስጥ የሌሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ የደጋ እሾህ አልባ የግራር ዛፎችን በመትከል እያላመደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የግርጫ የደጋ ፍራፍሬና  አትክልት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር / ዘነበ መኮንን  በዕለቱ የጽድ የባህር ዛፍ፣ የግራርና ዝሆኔ ሳር  ችግኞች ተከላ እንደተከናውነና ችግኞቹ የአካባቢ መራቆትን የሚቀንሱ  ምርታማነትን ለማሳደግ የሚችሉ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡  / ዘነበ አክለውም ምርምርር ማዕከሉን ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች ማስተዋወቁ ለቀጣይ ሥራ አዎንታዊ ምላሽ ለማግኘት ያስችላል ብለዋል፡፡

ከጨንቻ ከተማ አስተዳደር ከቆጎታ ወረዳ አስተዳደርና እና ከጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የመጡ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ሲሆን  ዩኒቨርሲቲው አካባቢውን በተለያየ መንገድ እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረው አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ሁሉ ከኒቨርሲቲው ጎን ለመቆም ቃል ገብተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

 

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /ቤት