የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ኢ-መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች የ2018 ትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ እሁድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ትምህርት መጀመሪያ ረቡዕ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- 

የ2018 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት (አዲስ) ተማሪዎች እንዲሁም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያጠናቀቁና የትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች መግቢያ ከትምህርት ሚኒስቴር የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መረጃ እንደደረሰን ወድያውኑ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

በ2017 ትምህርት ዘመን 1ኛ ዓመት ትምህርት አጠናቀው ትምህርት ክፍል ምደባ ያላገኙ ተማሪዎች ትምህርት ክፍል ምርጫ ሰኞ መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ምደባ የሚፈጸመው ማክሰኞ መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ውጤት የሚገለጸው ረቡዕ መስከረም 07 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡

ሁሉም የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት በኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል አስተባባሪነት የሚሰጠውን የ e-SHE SSS ሥልጠና በማጠናቀቅ ቢያንስ አንድ (1) ሰርተፊኬት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት