ወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ ከአባታቸው አቶ ኃይሉ ሐጎስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ገነት ክበበው ጥቅምት 2/1968 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ወ/ሮ መቅደስ ከአርባ ምንጭ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ10+2 በሴክሪተያል ሳይንስ ታህሳስ 30/2001 ዓ/ም የተመረቁ ሲሆን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ሰኔ 26/2006 ዓ/ም በማኔጅመንት የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ከተቀላቀሉበት ከታህሳስ 20/1993 ዓ/ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲውን በተለያዩ የሥራ መደቦች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ በዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ኃብት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሥር የሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ በመሆን ሕይወታቸው አስካለፈበት ዕለት ድረስ በታማኝነትና በቅንነት ተቋሙን ሲያገለገሉ ቆይተዋል፡፡
ወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ በተወለዱ በ50 ዓመታቸው መስከረም 18/2018 ዓ/ም በድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባለደረቦች እንዲሁም ለመላው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ