የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም በዙሪያው የሚገኙ ሕዝቦችን ባህልና ቋንቋ ለማልማት እና ለማስተዋወቅ በሥነ ጽሑፍ፣ ትወና፣ ሙዚቃ/ድምጻዊነት፣ የሙዚቃ መሣሪያ/ ቤዝ ጊታር፣ ሊድ ጊታር፣ ሳክስፎን፣ ኪቦርድ፣ ድራም፣ ዋሽንት፣ መስንቆ እና ክራር/ ተጫዋችነት፣ ውዝዋዜ/ዳንስ፣ ሰርከስ እና ሥዕል ዘርፎች ተሰጥኦ ያላቸውን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ታዳጊዎች በመመልመል በባለሙያዎች ታግዘው ለሕዝብ እይታ እድል የሚያገኙበትን መድረክ ለመፍጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የኪነ ጥበብ ተሰጥኦና የበጎ ፈቃድ ፍላጎት ያላችሁ በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ ከታች የተቀመጡ የምዝገባ አማራጮችን ተጠቅማችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን፡፡

የመመዝገቢያ አማራጮች

1.  የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች …………. በየካምፓሶቻችሁ የተማሪ ኅብረት /ቤት

2.  የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች    …………. ጫሞ ካምፓስ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም በአካል በመገኘት

3.  ኦንላይን/Online/ ለምትመዘገቡ ሊንኩን በመጫን የመመዝገቢያ ቅጹን መሙላት ትችላላችሁ፡-

https://docs.google.com/.../1FAIpQLSe2qdonr0m.../viewform...

ለተጨማሪ መርጃ በስልክ ቁጥር 0916831245 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA