አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 1.75 ሚሊየን ብር በጀት በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ የቱሪዝም ጸጋዎችን በተሻለ መልኩ ማልማት የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት የካቲት14/2018 / በላሃ ከተማ አስጀምሯል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የምርምርና ትብብር /ፕሬዝደንት ተወካይ / ተስፋዬ /ማርያም መሎ ኮዛ ወረዳ በርካታ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች ያሉት በመሆኑ  ቱሪዝምን ማልማት፣ ማስተዋወቅ እና መጠቀም የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት ቀርጾ ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል። የበርካታ ማዕድናት እና የቱሪዝም መዳረሻ የሆነው መሎ ኮዛ ወረዳ ለዩኒቨርሲቲው የሳውላ ካምፓስ መምህራንና ተመራማሪዎች የተሻለ የምርምር ስፍራ መሆኑንም አክለዋል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳመነ ቦጋለ ቱሪዝም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ የኢኮኖሚ ምንጭ ከመሆኑ ባሻገር ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት የላቀ ሚና አለው ብለዋል። መሎኮዛ ወረዳ በርካታ ያልተነኩ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችና ጸጋዎች ባለቤት መሆኑን በቂ የጥናትና ምርምር በማካሄድ ማረጋገጥ መቻሉንና በቀጣይ ሀብቱን በአግባቡ ለማልማት ፕሮጀክቱ መጀመሩን ገልጸዋል። ቱሪዝም  ከሥራ ፈጠራ ጋር የሚቆራኝ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳመነ የወረዳው አመራር አካላት፣ ማኀበረሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ ናቸው ብለዋል። መሠረተ ልማት፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎ፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲሁም የቱሪዝም ሀብቶቹን ማስተዋወቅ እና ሌሎች ተግባራት በቀጣይ የሚከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የጎፋ ዞን /አስተዳዳሪና የሥራና ክሂሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤሊያስ የቱሪዝም ዘርፍ ለሀገር እድገት ትልቅ አቅም ያለውና መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራበት መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም ለማኀበረሰቡ ተጠቃሚነት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን በጥናትና ምርምር ማስደገፍ አስፈላጊ መሆኑንና ከአካባቢው ጸጋዎች ተጠቃሚ ለመሆን በትብብር መሥራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ አውሳቶ ወረዳው የበርካታ ጸጋዎች ባለቤትና ሰፊ የኢኮኖሚ አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው ይህንን በአግባቡ ለመጠቀም ዩኒቨርሲቲው በዕውቀት የተደገፈ ምርምርና ድጋፍ እያደረገ እና ለማኅበረሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ የወረዳው መንግሥት የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት