
- Details
የሳይንስና ክፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ‹‹ወደ ዕውቀት መር ኢኮኖሚ›› በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያውን የትምህርት፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂና የኢንደስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን ከሐምሌ 5-8/2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካሂዷል፡፡ በኮንቬንሽኑ ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ሥራዎችን፣ ወደ ማኅበረሰብ የወረዱ የምርምር ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የኅትመት ውጤቶችን በማቅረብ ተሳትፎ አድርጓል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ሰኔ 14/213 ዓ/ም ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መልስ በዋናው ግቢ የችግኝ ተከላ በማካሄድ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መልስ የችግኝ ተከላ አካሄዱ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ዕቅድና ፕላን መምሪያ፣ አየር ንብረትና አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ፣ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ ከተማ ልማት፣ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት፣ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ጤና መምሪያ እና ጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ለተወጣጡ ባለሙያዎች በ‹‹GIS››፣ ‹‹GPS›› እና ሪሞት ሴንሲንግ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሰኔ 7-11/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል:: ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዩኒቨርሲቲው ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ ባለሙያዎች በ‹‹GIS››፣ ‹‹GPS›› እና ሪሞት ሴንሲንግ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ

- Details
የዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ማኅበረሰበሰ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከምራብ ዓባያና ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ግንቦት 14/2013 ዓ/ም የተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፊደላት፣ ድምጽና ስያሜያቸው እንዲሁም ተነባቢና አናባቢ ድምጾች በቃላት ውስጥ ሲገቡ የሚያመጡትን ለውጥ ለተማሪዎቹ የሚያስተምሩበት ስነ-ዘዴ በስፋት ተዳሷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ ከፌዴራልና ከደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ወረዳዎችና አርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የስፖርት ባለሙያዎችና የስፖርት መምህራን ከሰኔ 2-11/2013 ዓ/ም የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የ1ኛ ደረጃ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጠ