- Details
የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከደቡብ ኦሞ፣ ከሰገን አካባቢ ህዝቦች፣ ከወላይታና ከዳውሮ ዞኖች ለተወጣጡ ከ60 በላይ የጤና ጣቢያና የሆስፒታል ባለሙያዎች የስጋ ደዌ፣ የቲቢና የኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ከየካቲት 27 - መጋቢት 10 /2008 ዓ/ም ለአስር ቀናት በሁለት ዙር ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለመድኃኒትነት አገልግሎት በሚውሉ ሀገር በቀል ዕጽዋትና በሞሪንጋ /ሽፈራው/ ተክል ዙሪያ ሀገር አቀፍ ሲምፖዚዬም አካሂዷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡ Click here to see the News Video.
Read more: ለመድኃኒትነት በሚውሉ ዕጽዋትና በሞሪንጋ /ሽፈራው/ ተክል ዙሪያ ሀገር አቀፍ ሲምፖዚዬም ተካሄደ
- Details
የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በአንድ የዶክትሬትና በሁለት የማስተርስ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች የካቲት 12 እና 14 /2008 ዓ/ም ለሁለት ቀናት የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሂዷል፡፡
- Details
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባባር ከክልሉ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ለተወጣጡ 16 ሀኪሞች በሆስፒታሎች የደም አጠቃቀም ሥርዓትን ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና ከየካቲት 28 - መጋቢት 1/2008 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡
- Details
ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ከማህበራዊ ሳይንስና ሰነ ሰብ ኮሌጆችና ከህግ ትምህርት ቤት በ2008 የትምህርት ዘመን በአንደኛው ሴሚስቴር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች መጋቢት 23/2008 ዓ/ም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡