- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞንና ወረዳዎች ለተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖችና የዲቪዥን ኃላፊ ሴት አመራሮች የአመራርነት ሚናን ለማጎልበት ከኅዳር 19-20/2016 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የአመራር ምንነት፣ የጥሩ መሪ መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም ራስን፣ ቡድንና ተቋምን መምራት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖችና የዲቪዥን ኃላፊ ሴት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ጽ/ቤት እና ከምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ኅዳር 20/2016 ዓ/ም በዶርዜ ሆሎኦና ላካ ቀበሌ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል እንዲሁም በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚገኙ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የመስክ ምልከታና የዝርያ መረጣ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል እና በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚገኙ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ
- Details
በ2015 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት በማምጣት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
- Details
በ2016 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ለመማር አመልክታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁና የተመዘገባችሁ አዲስ አመልካች ተማሪዎች ፡-
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ተማሪ የሆኑት መቅደላይት ፈቃደ፣ ሰላማዊት ይብዛው እና ሜላት ገ/መድኅን ከግንቦት 29-30/2023 በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ በተካሄደው አምሳለ ፍርድ ቤት ውድድር ከሐሮማያ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ባሕር ዳር እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ጋር በመወዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ አሸናፊ ሆነው ለአህጉራዊ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንዲገኙ መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ


