ወ/ሮ አባይነሽ አጫ ከአባታቸው ከአቶ አጫ ጎማ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ግዞት ግዶ በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ታኅሣሥ 20/1981 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎፋ ዞን ጋልማ ሙሉ አንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሰላም በር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን ከሚሽን ኮሌጅ በአካውንቲንግ ሙያ በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡

ወ/ሮ አባይነሽ ከጥር 01/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ወ/ሮ አባይነሽ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 24/2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ወ/ሮ አባይነሽ አጫ የአራት ልጆች እናት ነበሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በወ/ሮ አባይነሽ አጫ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት