ዶ/ር ኢንጂነር አብደላ ከማል መሐመድ በ1997 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Hydraulic Engineering›› የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ1999 ዓ/ም በ ‹‹Hydraulic and Hydropower Engineering›› የትምህርት መስክ የሁለተኛ ዲግሪ፣ እንዲሁም ታኅሣሥ 2006 ዓ/ም ጀርመን ሀገር ሙኒክ ከተማ ከሚገኘው ‹‹Federal Armed University of Munich›› በ‹‹Water Resources Engineering›› የትምህርት መስክ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ከጥቅምት 22/2011 ዓ/ም እስከ ጥር 23/ 2011 ዓ/ም በጀርመን ከሚገኘው ‹‹Technical University of Munich›› ‹‹Short Term Researcher›› እንዲሁም ‹‹Leadership and Management››፣ ‹‹Participatory Workshop on Adaptive Capacity to Climate Change in the Upper Blue Nile Basin››፣ ‹‹Integrated modeling and assessment of water resources Management››፣ ‹‹International Certificate course on sediment transport and GSTARS computer modeling›› በተሰኙ ሌሎች ርእሰ ጉዳዮች ላይም አጫጭር ሥልጠናዎችን ወስደዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹Water Resources Engineering›› ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ በርካታ የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ኮርሶችን በመስጠትና ተማሪዎችን በማማከር ማስመረቅ ችለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማርና ምርምር ሥራዎች ባሻገር በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ዩኒቨርሲቲውን ያገለገሉ ሲሆን በዚህም ከታኅሣሥ 2000 ዓ/ም-የካቲት 2002 ዓ/ም የ ‹‹Hydraulic and water resources engineering›› ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፣ ከሰኔ 2007 ዓ/ም- ኅዳር 2010 ዓ.ም የውሃ ሃብት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር፣ እንዲሁም ከሰኔ 2007 ዓ/ም- ታኅሣሥ 2015 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንሲቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር አብደላ በተለያዩ የመስኖና የግድብ ፕሮጀክቶች ውስጥ በመሳተፍ ሙያቸውን በተግባር ያዋሉ ሲሆን ለአብነት ያህል ‹‹Senior Dam Design Engineer››፣ ‹‹Senior Hydrological modeler››፣ ‹‹Site Engineer and Coordinator›› በመሆን በተለያየዩ የንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ መስኖ እና ግድብ ሥራዎች ላይ በሙያቸው ተሳትፈዋል፡፡ ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚሠሩ የትብብር ሥራዎችን በማምጣትም በዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ተቋቁሞ እየሠራ የሚገኘው የውኃ፣ ውኃ ዲፕሎማሲና ኮሚዩኒኬሽን ፎረም አባል በመሆን በመስኩ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ሲሆን ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የሚገኘው ‹‹Ethiopian Journal of Water Science and Technology›› የምርምር ጆርናል ኤዲቶሪያል ማኔጀር በመሆን እየሠሩ ይገኛል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስምንት የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች አማካሪ፣ በስድስት የሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የውጭ ፈታኝ፣ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የውጭ ፈታኝ በመሆንም ሠርተዋል፤ እየሠሩም ይገኛሉ፡፡ ከ30 በላይ የሚሆኑ የምርምር ሥራዎቻቸውን በታወቁ የምርምር ጆርናሎች ላይ ማሳተም የቻሉት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከሐምሌ 8/2016 እስከ ኅዳር 7/2017 ዓ/ም በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነውም ሠርተዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል ከ1993 ዓ/ም ጀምሮ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ሆነው የሚያውቁትን በኋላም በመምህርነት፣ ተመራማሪነት እንዲሁም በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በትጋት ያገለገሉትን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው እንዲመሩ ከኅዳር 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት