የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት በሥሩ ከሚገኙ የሥራ የክፍል ኃላፊዎች ጋር በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ዛሬ ጥር 26/2017 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በሰጠው ተቆጥረውና ተለክተው የሚፈጸሙ ቁልፍ ተግባራት ላይ ዩኒቨርሲቲው ውል መግባቱን ገልጸው ለሥራው ስኬት ያለንን አቅም አሟጦ መጠቀምና በጋራ ተደጋግፎ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
አሳታፊ አስተዳደር በማስፈን እና በዕቅድ በመመራት ላቅ ያለ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የሕዝብን ሀብት ለተቋሙ ሁለንተናዊ ጥቅም ለማዋል እና ለዩኒቨርሲቲው ራእይና ተልዕኮ እውን መሆን ሁሉም ፈጻሚዎች በትኩረት መስራት እንደሚጠብቅባቸውም ም/ ፕሬዘደንቱ አውስተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ምንነት፣ ዓላማ፣ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት የቁልፍ ተግባራት አመልካቾች ድርሻ እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ እየታዩ ያሉ ችግሮች ላይ አጠር ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻና ውይይት ተደርጓል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት