በ2018 ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመረቃችሁ ተመራቂዎች በሙሉ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ትምህርት ዘመን በ2018 ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም ለተመረቁ 5 ተማሪዎች በ2ኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ፕሮግራም የትምህርት ዕድል አመቻችቷል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተመራቂዎች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የምዝገባ መስፈርቶች፡-
NGAT (National Graduate Admission Test) ያለፈ/ች
በ2018 ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም (Regular Program) የተመረቀ/ች
የአካዳሚክ አማካይ ውጤት (CGPA)፡-
ለወንዶች፡ 3.50 እና ከዚያ በላይ
ለሴቶች፡ 3.25 እና ከዚያ በላይ
የማመልከቻ ጊዜ፡- ከጥቅምት 16 እስከ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም ድረስ
የማመልከቻ ሁኔታ፡- በሚከተለው የፎርም ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፡
🔗 https://forms.gle/QkcePZiSyTPYtNX79
ማሳሰቢያ፡-
የውድድሩ ውጤት በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የሚገለጽ ይሆናል።
ያለፉ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፡ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ይሆናል።
የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ጽሕፈት ቤት

