አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ኢንተርፕራይዞችና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጆች ንዑስ ቀጠናዊ ትስስር  ፎረም ከታቀፉ ተቋማት ጋር 2017 በጀት ዓመት 3 ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የፎረሙ አባል ተቋማት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ገሮ ካምፓስ  ውይይት ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክተር / ቶሌራ ሴዳ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀናጀት ለሀገሪቱ የኢንደስትሪ ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ተቋማት በተናጥል ከመሥራት ወጥተው ቅንጅት ፈጥረው  ቢሰሩ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችል ታምኖበት ፎረሙ መመሥረቱን  / ቶሌራ አንስተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ኢንደስትሪ ትስስር አስተባባሪ / ሙሉጌታ ሐብቴ   የአካባቢው ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከዩኒቨርሲቲው ጋር የፈጠሩት ትስስር ክፍተቶቻቸውን ለመሙላትና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

የጋሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡቶ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክሂሎት የዳበሩና  የሠለጠኑ ዜጎች የሚፈሩባቸው ተቋማት መሆናቸውን ገልጸው ተቋማቱ እንደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካሉ የምርምር ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር መሥራታቸው ለተቋማቱ ውጤታማነት የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በዕለቱ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ /ዲንና የፎረሙ ጸሐፊ አቶ ወርቅነህ /ሚካኤል የፎረሙን 3 ሩብ ዓመት አፈጻጸምና የተከናወኑ ተግባራትን ጠንካራ ጎኖችን፣ የታዩ ክፍተቶችንና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ሪፖርት አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም የጋራ መግባባት ተደርሷል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት