በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ሥር የተመሠረተውን ‹‹AMU Tech HUB›› ክበብ አስመልክቶ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች ኅብረት ለነባር እና አዲስ ገቢ ተማሪዎች መስከረም 30/2018 ዓ/ም የማስተዋወቂያ እና የ2018 ዓ/ም ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ ዩኒቨርሲቲው ዕውቀት የሚፈልቅበት መሆኑንና ዕውቀቱም ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር በቴክኖሎጂና ሥራ ፈጠራ የታገዘ ሊሆን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ ያለውን ጊዜያቸውን በአግባቡና ሥራን በመፍጠር ማሳለፍ የሚጠበቅባቸው መሆኑንና ኢንስቲትዩቱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ኅብረት ዋና አፈ ጉባኤ እና የክበቡ መሥራች ተማሪ ሶፎንያስ መብራቱ ክበቡ ተማሪዎች ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ቴክኖሎጂን በተግባር እንዲጠቀሙና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የሚታየውን ክፈተት ለመሙላት በማለም በ2017 ዓ/ም አጋማሽ መመሥረቱን አስታውሷል፡፡ ክበቡ የተማሪዎችን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ክሂሎት ከማሻሻል አንጻር ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን የጠቀሰው ተማሪ ሶፎንያስ ባሳለፍነው ዓመት በሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ዐውደርእይ ከማዘጋጀት እንዲሁም የተማሪዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ከማጠናከር አኳያ ሰፊ ሥራ መሠራቱን  ተናግሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ የኮምፒውተር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋከልቲ ዲን ተወካይ ዶ/ር ክብረአብ አዳነ፣ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምኅንድስና ፋከልቲ ተጠሪ ረ/ፕሮፌሰር መስፍን ጋዴታ፣ የ/አ/ም/ዩ ቤተ መጻሕፍት ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል እንዲሁም ነባር እና አዲስ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት