የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ‹‹AMU Tech HUB›› የተሰኘ የተማሪዎች ክበብ ምሥርታ መርሃ ግብር ሚያዝያ 8/2017 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮምፒዩቲንግና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋካልቲ ዲን መምህር ጌታሁን ትዕግሥቱ ክበቡ የቴክኖሎጂ ፍላጎት ባላቸው ተማሪዎች የተመሠረተ ሲሆን ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው በመደጋገፍ የቴክኖሎጂ ክሂሎታቸውን እንዲያጎለብቱ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ አበበ እንደገለጹት ‹‹AMU Tech HUB Club›› ሁሉም የቴክኖሎጂ ተማሪዎች የሚሳተፉበትና ትልቅ ሥራ የሚጠበቅበት በመሆኑ ተማሪዎች የክለቡን ዓላማ ለማሳካት በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡
የተማሪዎች ኅብረት አፈ ጉባኤ ተማሪ ሶፎንያስ መብራቱ እንደገለጸው ክበቡ የተመሠረተው በተማሪዎች ኅብረት አማካኝነት ሲሆን ተማሪዎች ቴክኖሎጂን ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር በተግባር እንዲጠቀሙና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የሚታየውን ክፈተት መሙላትን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ክበቡ በራሱ መመሪያና ደንብ የሚተዳደርና የተማሪዎችን የቴክኖሎጂ ፈጠራ የሚደግፍና የሚያበረታታ መሆኑንም አፈ ጉባኤው አስረድቷል፡፡
የክበቡ ፕሬዝደንት ተማሪ ታማኝ ዘውዱ በበኩሉ ክበቡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን የቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ራዕይ ሰንቆ የተመሠረተ ሲሆን ማንኛውም በዘርፉ ላይ ፍላጎትና ተሰጥኦ ያለው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ የክበቡ አባል መሆን እንደሚችል ተናግሯል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_universit
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት