የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በሥሩ ከሚገኙ የሥራና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር በ2017 ዓ.ም የሚተገበር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ጥር 7/2017 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የጫሞ ካምፓስ ኃላፊና የኮሌጁ ዲን ዶ/ር መስፍን መንዛ የቁልፍ ተግባራት ፊርማው ዋና ዓላማ ተቆጥሮና ተለክቶ የተሰጠውን ሥራ በየጊዜው በዕቅድ መሠረት ክትትል እያደረጉ እንዲፈጽሙ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር መስፍን ፊርማው በተዋረድ ባሉ የሥራ ክፍሎች የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው እንደ ኮሌጅ ለዕቅዱ ስኬት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያድርጉ አመላክተዋል፡፡
የኢኮኖሚክስ ት/ክፍል ኃላፊ መምህር ሙሉጌታ ፈቃደ በተፈራረምነው ውልና በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት በሥራችን ያሉ ሠራተኞችን አስተባብረን የተጣለውን ግብ ለማሳካት እንተጋለን ብለዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት