በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ሆርቲካልቸር ት/ክፍል ‹‹Causes of Postharvest Losses of Horticultural Crops in Ethiopia›› በሚል ርእስ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ጥር 14/2017 ዓ/ም ሴሚናር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ዋና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ተወካይ ዶ/ር ተስፋዬ ሀ/ማርያም እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግሥት አቅጣጫ በማስቀመጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሠራ ሲሆን በድኅረ ምርት ብክነት ምክንያት የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ኪሳራ በመቀነስ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ኢኮኖሚን ማሳደግ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ዩኒቨርሲቲው የድኅረ ምርት ብክነትን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካትን በማሳተፍ ግንዛቤ ለመፍጠር ሴሚናሩን ማዘጋጀቱን ዶ/ር ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደግፌ አሰፋ በበኩላቸውበዋናነት ጋሞ ዞን ፍራፍሬና አትክልት በብዛት የሚገኝበት አካባቢ እንደመሆኑ ከአመራረት ጀምሮ እስከ ገበያ ድረስ ያለውን ብክነት መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ችግሮችን ለይቶ መፍትሔ ለመስጠት  ሴሚናሩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የሆርቲካልቸር ት/ክፍል ኃላፊ መ/ር ዘርይሁን ሻምበል ኢትዮጵያ በዓለም የምግብ ዋስትና ችግር ከሚታይባቸው ሀገሮች መካከል አንዷ ስለሆነች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር ባሻገር የምግብ ብክነትን ለመቀነስ በትኩረት መሥራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ 

የሴሚናሩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከሴሚናሩ ትልቅ ግንዛቤ ማግኘታቸውንና መነቃቃት እንደፈጠረላቸው ተናግረው በአካባቢው የተለያዩ የፍራፍሬና የአትክልት ምርት ቢኖርም በበሽታ፣ በምርት ማነስ እና በምርምርና በግብርና ኤክስቴንሽን ያልተደገፈ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በዕውቀትም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ድጋፉን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት