በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጫሞ ካምፓስ በ2017 ዓ.ም ለተመደቡ የማኅበራዊ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲንና የካምፓሱ ኃላፊ ዶ/ር መስፍን መንዛ ከዚህ ቀደም በተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በአብዛኛው አመርቂ ውጤት በማምጣት ማለፍ እንደቻሉ ገልጸው ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርታቸው እና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ መደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ተሻግረው መቀጠል እንዲችሉ እንደ ካምፓስ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግም ዲኑ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የኮሌጁ ዲን፣ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን፣ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የተማሪዎች ኅብረት እና የሰላም ፎረም አባላት የተገኙ ሲሆን የተማሪዎች የዲሲፕሊን ሕጎች፣ በሁሉም ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶች እና በግቢው የሚኖራቸውን  ቆይታ በሚመለከት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት