አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በመጪው ግንቦት ወር ላይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደውን የውኃና ሃይድሮ ዲፕሎማሲ ፎረም አስመልክቶ በሚካሄደው የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጥያቄና መልስ ወድድር ላይ ለሚሳተፉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች ሚያዝያ 25/2017 ዓ/ም ወድድሩን አስመልክቶ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ታምሩ ተሰሜ በዩኒቨርሲቲያችን የሚካሄደውን ፎረም አስመልክቶ አርባ ምንጭ ከተማ ከሚገኙ አምስት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ውኃና የውኃ ዲፕሎማሲን የተመለከተ የጥያቄና መልስ ወድድር የሚካሄድ በመሆኑ ከት/ቤቶቹ ለተወጣጡ 10 ተማሪዎች በውድድሩ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ በውድድር መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጭምር ይገኙበታል ያሉት ዶ/ር ታምሩ ውድድሩ በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ የሚተላለፍ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የውድድሩ አሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን ተወዳዳሪዎች ከሽልማቱ ባሻገር የከተማቸውን ብሎም የትምህርት ቤታቸውን ስም ለማስጠራት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በገለጻው የተሳተፉ ተማሪዎች ከመርሃ ግብሩ ለውድድሩ የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኙበት መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ለውድድሩ ብቁ ለመሆን አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከጫሞ፣ ከጋሞ ባይራ እና ከፊውቸር ሆፕ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎች ይሳተፋሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት