ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት ከኅዳር 9 - 15/2017 በመላው ዓለም ይከበራል። ይህን ታሳቢ በማድረግ የአምዩ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አዘጋጅቷል።
ስለሆነም የቢዝነስ ሃሳብ ያላችሁ ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) https://forms.gle/ayoEzKtEYfWHQ35MA በመጫን እንድትመዘገቡ እየጋበዘን ሃሳባችሁን በግልም ሆነ በቡድን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለአሸናፊዎች የማበረታቻ ገንዘብ እና የምስክር ወረቀት የምንሸልም መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
• የምትወዳደሩበት የቢዝነስ ሃሳብ ከዚህ በፊት ተወዳድራችሁበት ሽልማት ያገኛችሁበት መሆን የለበትም
• ውድድሩ አሁን በትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ብቻ የሚመለከት ይሆናል
• የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 28/2017 እስከ ኅዳር 5/2017 ዓ.ም ነው
የአምዩ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት