የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ሪጂን ጋር በመተባበር ለኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር ተማሪዎች እና ለእናት መቀነት ተጠቃሚዎች በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎትና በሥሩ የሚገኙ የተለያዩ ሥራዎችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሚያዝያ 25/2017 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ሠናይት ሳህሌ እንደገለጹት ኢትዮ ቴሌኮም  ለተከታታይ ዓመታት በዩኒቨርሲቲው የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ 210 ተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በመጀመሪያ ዓመት ለተለያዩ ችግሮች እንዲጋለጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ የኢኮኖሚ አቅም ማነስ መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሪት ሠናይት ኢትዮ ቴሌኮም ይህን ችግር ለመቅረፍ እያደረገ ያለው ድጋፍ  የሚያስመሰግን መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ሪጅን የመጡት አሠልጣኝ አድማሱ ቡሩሶ ሥልጠናው በዋናነት ሠልጣኞች የኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር እንደመሆናቸው የተቋሙን ራዕይ፣ ተልእኮና እሴት እንዲሁም አገልግሎቱን በተመለከተ ግንዛቤ አግኝተው የአካባቢውን ማኅበረሰብ ስለተቋሙ አገልግሎት እንዲያሳውቁ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት