የሰላም ሚኒስቴር፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘውን የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት /የፋሲለደስ ስምምነት/የሚሰኘውን ውል በዩኒቨርሲቲው  ለማስቀጠል ያለመ የቃልኪዳን ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል የፋሲለደስ ስምምነት የዩኒቨርሲቲው ሠራተኛ እና የከተማው ማኅበረሰብ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመድበው ከሚመጡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች አንድ አንድ በመምረጥ እስኪመረቁ ለተማሪዎቹ የተለያዩ እገዛዎችን በማድረግ፣ በዓላትን በጋራ በማሳለፍ የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት ቤተሰባዊ ግንኙነትን መፍጠር የስምምነቱ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ከተለያዩ አካባቢ የሚመጡ በመሆኑ የሚፈጠረው ቤተሰባዊ ግንኙነት ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ሕዝብ ለሕዝብ ትውውቅ እንዲሁም ለማኅበራዊ እሴት ግንባታ እንዲሁም በተማሪዎቹ ዘንድ የUገር ፍቅርን ከማሳደግ አኳያ ጉልህ  ሚና የሚጫወት መሆኑን የሚገልጹት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘውን የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችና ከተሞች እንዲስፋፋ ለማድረግ በሰላም ሚኒስቴር አነሳሽነት ከዩኒቨርሲቲው እና ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም አዲስ ከሚመጡ ተማሪዎች የተወሰኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራንን በማሳተፍ በሙከራ ደረጃ ሥራው በዩኒቨርሲቲው የሚጀመር መሆኑን ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት