የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር ድጋፍ ለማድረግ ውይይት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በጉዳዩ ላይ ተወያይቶበት ለካውንስሉ የድጋፍ የመነሻ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን የካውንስሉ አባላትም በቀረበው የመነሻ ሃሳብ ላይ በመስማማት ለግድቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ስምምነታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይ የዩኒቨርሲቲውን መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችን በማወያየት ተቋማዊ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡ 

በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል ስለ ግድቡ አሁናዊ ሁኔታና ቀሪ ሥራዎችን አስመልክቶ ገለጻ አቅርበዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት