አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ  ለተጎዱ ወገኖች ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የደራሽ ምግብና የአምስት መቶ ሺህ ብር የጥሬ ገንዘብ ሰብዓዊ ድጋፍ አድርጓል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በዩኒቨርሲቲው  የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን  የተመራው የልዑካን ቡድን በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውንና ሕይወታቸውን ያጡ ተጎጂዎች ቤተሰቦችን በስፍራው ተገኝተው  አጽናንተዋል።

በአካባቢው  በተፈጠረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅና ልባዊ ሐዘን በራሳቸውና በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ስም የገለጹት ምክትል ፕሬዝደንቷ ለሁሉም ቤተሰቦችና ለመላው የአካባቢው ነዋሪዎች መጽናናትን ተመኝተዋል። በቀጣይም ማኅበረስቡን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረግ ጥረት ውስጥ ዩኒቨርሲቲውና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ወ/ሮ ታረኳ ገልጸዋል።

የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ፣ የሳውላ ካምፓስ ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ጫሜኖ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማጽናናት በስፍራው ከተገኙ መካካል ናቸው።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት