የዩኒቨርሲቲው ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኮሌጁ የሚገኙ አራት የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ የውስጥ ግምገማ ሐምሌ 22/2017 ዓ/ም አካሂዷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ሜዲስን እና አንስቴዥያ ግምገማ የተደረገባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ናቸው።
የዩኒቨርሲቲዉ የጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤፍሬም ጌታሁን ኮሌጁ በዚህ ዓመት በሁለት ፕሮግራሞች ሀገር አቀፍ አክሪዲቴሽን ማግኘቱን አስታውሰው በሥርዓተ ትምህርቶች ላይ የሚደረጉ ክለሳዎች ወቅቱ የሚፈልገውን ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ለማፍራት አጋዥ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ኮርፖሬት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር በላይ ቦዳ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ መካሄዱ ውጤታማ የማስተማር ስልቶችን እንዲሁም ግብዓቶችን በማምጣት የማስተማር ልምዶችን ለማሻሻል አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል። ሥርዓተ ትምህርቶች ሲከለሱ ለተማሪዎች ፍላጎት እና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ምሩቃንን ማፍራት ላይ ማተኮር እንደሚገባና ሥርዓተ ትምህርቶችን በየጊዜው የመከለስ ልማድ ሊዳብር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ዳይሬክተር አቶ አብነት ተሾመ በግምገማ ሂደቱ ለሥርዓተ ትምህርቶቹ መሻሻል የሚረዱ ገንቢ አስተያየቶች ከመድረኩ ማግኘት እንደተቻለ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት