በዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ አዘጋጅነት ከታኅሣሥ 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ በየካምፓሱ በሚገኙ ወንድ ተማሪዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አንተነህ ዘርይሁን እንደገለጹት ታኅሣሥ 14/2017 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት ዋናው ግቢ ከነጭ ሣር እንዲሁም አባያ ካምፓስ ከኩልፎ ካምፓስ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ሲሆን ታኅሣሥ 16/2017 ዓ/ም ጫሞ ካምፓስ ከኩልፎ ካምፓስ እንዲሁም ዋናው ግቢ ከአባያ ካምፓስ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ በ2ኛው ዙር ጨዋታ ታኅሣሥ 18/2017 ዓ/ም ነጭ ሣር ካምፓስ ከአባያ ካምፓስ፣ ጫሞ ካምፓስ ከዋናው ግቢ እንዲሁም ታኅሣሥ 20/2017 ዓ/ም ኩልፎ ካምፓስ ከዋናው ግቢ እና ነጭ ሣር ካምፓስ ከጫሞ ካምፓስ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ መምህርና የውድድር ኮሚቴው አባል አቶ ቴዎድሮስ ካሴ ውድድሩ ተቀዛቅዞ የቆየውን የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መነቃቃት ለመፍጠር፣ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የተማሪዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የተሻለና የተጠናከረ እንዲሆን ለማስቻል እንዲሁም ዩኒቨርሲቲውን በመወከል በሀገር አቀፍ ውድድሮች የሚሳተፉ ብቁ ተጫዋቾችን ለመለየት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

በጨዋታው መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በአባያ ካምፓስ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ የአባያ ካምፓስ ቡድን የጫሞ ካምፓስ አቻውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ በተመሳሳይ በኩልፎ ካምፓስ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ  ኩልፎ ካምፓስ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት የነጭ ሣር ካምፓስ አቻውን መርታት ችሏል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት