ወ/ሪት ከበቡሽ ዋልጬ ከአባታቸው ከአቶ ዋልጬ መንገሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ካንኤ ዳረቴ በ1978 ዓ.ም በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ደጋ ኦቾሎ ቀበሌ ተወለዱ::

ወ/ሪት ከበቡሽ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በደጋ ኦቾሎና በጫኖ ሚሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት የተከታተሉ ሲሆን ከዙማ ኮሌጅ በክሊኒካል ነርስ 10+3 ዲፕሎማ ነሐሴ 30/2001 ዓ/ም ተመርቀዋል፡፡

ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ መደቦች ተቀጥረው ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሪት ከበቡሽ በተማሪዎች አገልግሎት ክሊኒክ ጁኒየር ክሊኒካል ነርስ እንዲሁም ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ቺፍ ነርስ በመሆን ተቋሙን አገልግለዋል፡፡

ወ/ሪት ከበቡሽ ዋልጬ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ39 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሪት ከበቡሽ ዋልጬ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት