የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ከሳውላ ካምፓስ ኃላፊ ጋር በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራርመዋል፡፡
በም/ፕሬዝደንት ማዕረግ የሳውላ ካምፓስ ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ጫሜኖ በዩኒቨርሲቲው ተቆጥረውና ተለክተው እንደ ካምፓስ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የተሰጡንና ቁልፍ ተግባራት ለመፈጸም በመስማማት ተፈራርመናል ብለዋል፡፡
ቁልፍ ተግባራት ላይ በትኩረት መሥራት አለብን ያሉት ኃላፊው የተሠሩ ሥራዎች በአግባቡ ተለቅመውና የሪፖርት አካል ተደርገው መቅረብ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ከትምህርት ክፍልና ከአስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማካሄድ የውል ስምምነቱን እስከ ታችኛው ፈጻሚ አካል ድረስ በማውረድ ለተግባራዊነቱ እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት