አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 2017 የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸምን (KPI) የገመገመ ሲሆን በሌሎች ትኩረት በሚሹ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያም ዛሬ የካቲት 27/2017 / ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር የጋራ ውይይት አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁልፍ ተግባራት ውል ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ከም/ፕሬዝደንቶች፣ /ፕሬዝደንቶች ከስራቸው ከሚገኙ መዋቅሮችና የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውል መግባታቸውን አስታወሰዋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲያችን የተሰጡ ቁልፍ ተግባራት ተቆጥረውና ተለክተው እስከታችኛው መዋቅርና ግለሰብ ድረስ መውረዳቸውን ማረጋገጥ፣ የቁልፍ ተግባራቱ አፈጻጸም እስከ አሁን የደረሰበትን ደረጃ መፈተሸ፣ የተግባራቱን አፈጻጸም የሚከታተል አሠራር መዘርጋቱን ማረጋገጥ እንዲሁም ግቦቹ በታቀደላቸው ጊዜ ውስጥ መፈጸም መቻለቸውን መፈተሸ የዕለቱ የግምገማ መድረክ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የኮሌጅና  የኢንስቲትዩት ዲኖች፣ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣ የአካዳሚክና አስተዳደር ዳይሬክተሮች በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ጥናት፣ በማኅበረሰብ ጉድኝት፣ በዓለም አቀፋዊነትና አስተዳደር ዘርፎች ከቁልፍ ተግባራት አንጻር ያከናወኗቸውን ተግባራት የአፈጻጸም ደረጃ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በውይይት መርሃ ግብሩ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና እስተያየቶች ተነስተው ከሚመለከተው አካል ምላሽ የተሰጠበት ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት በትኩረት ሊሰራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት