በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአገራዊ የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test - NGAT) ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች በሙሉ፣ ፈተናውን በተመለከተ የሚከተሉትን አስፈላጊ መረጃዎች በጥንቃቄ እንድትመለከቱ እናሳስባለን።

1. የቀን፣ የሰዓትና የፈተና ቦታ መረጃ

  • የፈተና ክፍል ማወቂያ ዝርዝር፦ ነሐሴ 18/2018 .. ከቀኑ 230 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋና መግቢያ በር ላይ ይለጠፋል።
  • የፈተና መስጫ ቦታ፦ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ
  • የፈተና ቀን፦ ረቡዕ፣ ነሐሴ 20/2018 .. እና ሐሙስ ነሐሴ 21/2018 ዓ/ም
  • የፈተና መጀመሪያ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 200 ጀምሮ

2. ማሳሰቢያ

  • የፈተና መግቢያ ካርድ፦ የፈተና መግቢያ ካርድ ከሲስተሙ ማውረድ ስለተፈቀደ፣ በተመዘገባችሁበት የግል አካውንት በመግባት የፈተና መግቢያ ካርዳችሁን ማውረድና ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ።
  • ሕጋዊ መታወቂያ፦ ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ።
  • የተከለከሉ ዕቃዎች፦ ወደ ፈተና ጣቢያ ሞባይል ስልክ፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር እና ሌሎች የተከለከሉ ዕቃዎችን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ድኅረ-ምረቃ ት/ቤት