አርባ ምንጭ (ነሐሴ 12 ቀን 2018 .) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድን ባለሥልጣን የጋራ ትብብር በማሌ፣ በአሌ እና በመሎኮዛ የተካሄደውን የማዕድን አለኝታ ጥናት የምርምር ውጤት ለማረጋገጥ የተዘጋጀው የምርምር ውጤት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (Mineral Potential Research Validation Workshop) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ተካሂዷል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / አብደላ ከማል እንደገለጹት፣ ማዕድን እንደ ሀገር ትኩረት ከተሰጣቸው 5 የልማት ዋልታዎች ወይም ምሶሶዎች መካከል አንዱ መሆኑን አብራርተዋል። በዘርፉ ላይ እንደ ሀገር የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት መነሻ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ዘርፉን በምርምርና ጥናት ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ሀገር በማዕድን ረገድ ትልቅ አቅም እንዳለ የጠቆሙት ፕሬዝደንቱ፣ ሀገሪቱ ያላትን የማዕድን ሀብቶች በአግባቡ እንድትጠቀምና የውጭ ምንዛሬ ከዘርፉ እንድታገኝ ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን የተቀናጀ ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

 

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር /ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ በበኩላቸው፣ እንደ ዩኒቨርሲቲ የሚደረጉ የምርምርና ጥናት ሥራዎች በዓይነት፣ በቁጥርና በጥራት እያደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው የምርምር ሥራዎች የሀገሪቱን የልማት የትኩረት አቅጣጫዎችና የቅድሚያ ትኩረቶች መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በዕለቱ የቀረቡትን የማዕድን አለኝታ ጥናቶች እንዲሁም በእንሰት ላይ የሚደረጉ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለአብነት አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የሚገኘው የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል ትልቅ አቅም ያለው በመሆኑ፣ ክፍሉ ከእስከዛሬው የተሻሉ የምርምር፣ የጥናትና የማማከር ሥራዎችን እንዲሰራ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ከክልሉ ማዕድን ባለሥልጣን ጋር የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትና የጥናት ቡድኑ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሄለን ዮሐንስ  ለማዕድን ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ እንደ ሀገር ትልልቅ እምርታዎች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ክልሉም ለዘርፉ ዕድገት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በባለሥልጣን ደረጃ ቢሮ በማቋቋም በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በክልሉ የጌጣጌጥ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉና ለግንባታ የሚሆኑ ሰፊ የማዕድን ክምችቶችና ጸጋዎች ያሉት ሲሆን፣ ይህን ዕምቅ አቅም ወደ ገቢ ለመቀየር በምርምርና በዳታ የተደገፈ ሥራ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። በቀጣይም የበለጠ መስራት እንደሚገባ በመጠቆም ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ እና የአማካሪዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ቦሻ ቦምቤ፣ መንግሥት ማዕድንን አንዱ የልማት ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው የሀገሪቱ የልማት አቅጣጫ በግብርና መር ኢንዱስትሪ ላይ ብቻ ያተኮረ እንደነበር ያስታወሱት ዶክተር ቦሻ፣ አሁን ላይ ግን የልማት አቅጣጫው ከአንድ ወደ አምስት ዋና ዋና ምሶሶዎች በመሸጋገሩ ብዝሃ-ኢኮኖሚ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ከእነዚህ አምስት የልማት ምሶሶዎች አንዱ ማዕድን በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ለሀገሪቱ GDP ጭምር ድርሻ ማበርከት መጀመሩን ገልጸዋል። እስካሁን በዘርፉ ብዙ ያልተሰራ በመሆኑ ሁለቱ ተቋማት የጀመሩት ሥራ የሚደነቅ መሆኑንና ወደፊትም ክልሉም ሆነ ሀገሪቱ ከዘርፉ እንድትጠቀም ሥራዎች ይበልጥ ሰፍተው መስራት እንዳለባቸው እና የዘርፉን ሀገራዊ ራዕይ ማሳካት እንደሚቻል አስረድተዋል።

 

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር / ቶሌራ ሴዳ እንደተናገሩት፣ የተሰራው ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወነ ትልቅ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ከክልሉ ጋር 2009 . ጀምሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም 11 የማዕድን አለኝታ ጥናቶችን በስኬት አጠናቆ ማስረከቡን አብራርተዋል። ዩኒቨርሲቲው ለማዕድን ዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተወጣ እንደሆነና በዩኒቨርሲቲው የጥናት ውጤት ላይ ተመስርተው ወደ ልማት በመግባት ሀገርንና ማህበረሰብን መጥቀም የጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ገልጸዋል። የክልሉ ማዕድን ባለሥልጣን 2009 . ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር የሚሰራቸው ሥራዎች ለሌሎች ሴክተሮችም አርአያ ወይም ምሳሌ የሚሆኑ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

 

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው እና የባለሥልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ የየወረዳዎቹ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምርምር ግኝቶቹ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዚህም በወርክሾፑ በጥናት ቦታዎቹ የተገኙ የማዕድን ዓይነቶች፣ ጥራታቸው እና በቀጣይ መወሰድ የሚገባቸው የምክረ-ሐሳብ አቅጣጫዎች በጥናት ቡድኑ ተወካይ ተመራማሪዎች አገኘሁ ቦርኮ፣ አስማማው ሀነግባይና እና ሰውአገኝ የኔሰው በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ የመድረኩን ፍጻሜ ተከተሎም የጥናቱን ዝርዝር የምርምር ሰነዶች የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድን ባለሥልጣን አስረክበዋል።

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /ቤት