የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የዩኒቨርሲቲውን 2017 / የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሚያዝያ 20/2017 / ገምግሟል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሶስቱ የዩኒቨርሲቲው ዋነኛ ተልዕኮዎች አንጻርና በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጡ ቁልፍ ተግባራትን ለመተግበር በርካታ ሥራዎችን መስራቱን ተናግረዋል፡፡ / / አብደላ በሁሉም ዘርፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ተግባራዊ የማድረግ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝብው በቀሪ ጊዜያት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተብለው በሪፖርቱ የተመላከቱ አበይትና ቁልፍ ተግባራትን ለመፈጸም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ይፍሩ በመማር ማስተማር፣ ምርምር ማኅበረሰብ ጉድኝት፣ ዓለም አቀፋዊነትና አጋርነት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በሪፖርታቸው ዳሰዋል፡፡ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች እውቅና እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ፣ 3 ዲግሪ ተማሪዎችን ያካተቱ ጥናትና ምርምሮች እየተካሄዱ መሆናቸው፣ ለመምህራን በግራንት ፕሮጀክት አጻጻፍ ላይ ሥልጠና መሰጠቱ፣ እንዲሁም የማኅበረሰቡን ነባራዊ ችግሮች የሚፈቱ ልማታዊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አቶ ሰለሞን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በዕለቱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ አበበ ‹‹e-learning›› እና የ5 ሚሊየን ኮደርስን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ አድርገዋል። ዶ/ር መሐመድ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው ዲጅታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ እንዲሁም ‹‹e-learning›› እና የ5 ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን ከመፈጸም አንጻር ለመምህራንና ተማሪዎች የዲጂታል ሊትረሲ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ለሥራው የሚያግዙ ግብአቶችን የማሟላት ሥራም እየተሰራ እንደሚገኝና እስከ አሁን ያለው የዘርፉ አፈጻጸም በቀጣይ ብዙ ሥራ የሚጠበቅ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑንም በሪፖርታቸው አመላክተው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው መምህራን ተማሪዎችና ሠራተኞች የዲጂታል ሊትረሲ አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባና በ5 ሚሊየን ኮደርስ የሚሰጠውን ስልጠና እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ ሪፖርቱን የተመላከቱ ጥያቄና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት