በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ ‹‹Operations Research›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ስሜነህ ሁናቸው የመመረቂያ ጽሑፍ ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ዕጩ ዶ/ር ስሜነህ ሁናቸው የመጀመሪያ ዲግሪውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Applied Mathematics›› እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Mathematics Optimization›› ያገኘ ሲሆን 3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Dynamic Vehicle parking Pricing Prediction of Demand and Optimal Selection of Parking Lots›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡
የዕጩ ዶ/ር ስሜነህ ሁናቸው ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት