በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹Biology›› ት/ክፍል በ ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር መሐመድ ሰኢድ  የመመረቂያ ጽሑፍ ጥር 2/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር መሐመድ ሰኢድ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Natural Resource Management›› ትምህርት እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Range Ecology and Biodiversity›› ትምህርት ያገኘ ሲሆን  3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹ The Role of Area Enclosure in Vegetation Restoration, Carbon Storage Potential, and land Use land Cover Change, Central Rift Valley, Ethiopia›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር መሐመድ ሰኢድ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት