የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት በሥሩ የሚገኙ የሥራ ክፍሎችን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በመርሃ ግብሩ ሁሉም ሥራ አስፈጻሚዎችና ዳይሬክተሮች የሥራ ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በሥራ ክፍሎቹ የታቀዱ ተግባራት የተፈጸሙበትን ደረጃ ለመፈተሽ፣ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት መፍትሔዎችን ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

ቀጣይ ሥራዎች ዕቅድን በመከለስ ጭምር የዩኒቨርሲቲውን የሪፎርም አጀንዳዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ተከትለው ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያስችል አቅጣጫ መስጠትና ግንዛቤ መፍጠር ሌላኛው የመርሃ ግብሩ ዓላማ መሆኑንም ኃላፊዋ አክለዋል፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት