በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ሐሙስ እና ዓርብ ኅዳር 25 እና 26 ቀን 2018 ዓ/ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚህ መሠረት በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ከታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ አባያ እና ጫሞ የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች፤ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡
ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement
ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አራት የፓስፖርት መጠን ያለው ጉርድ ፎቶ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

