አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ የኢኮኖሚክስ ትምህርት መስክ 4ኛ ዓመት የሳምንት መጨረሻ ተማሪ የነበረው ተማሪ ዋና ሳጅን መለሰ አባይነህ ከቡልቂ ወደ አደጋው ቦታ ተጎጂዎችን ለመርዳት በሄደበት አደጋው በድጋሚ በመከሰቱ በድንገት ሕይወቱ ያለፈ በመሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዞመዶቹና ጓደኞቹ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው በተለይ ለሳውላ ካምፓስ ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት