የአርባ ምንጭ ዩኒቪርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ‹‹Spiritan Community Outreach Ethiopia - SCORE›› በተሰኘ ፕሮጀክት ላይ ለሚሠሩ ባለሙያዎች በፕሮጀክት ማኔጀመንትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከኅዳር 25-28/2017 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል ፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
‹‹Project Meanings and Fundamentals››፣ ‹‹Project Life cycle and Project planning Issues››፣ ‹‹Project Monitoring and Evaluation›› እና ‹‹Reviewing Tools of Project Management›› የሚሉት ሥልጠናው ከተሰጠባቸው ርእሶች መካከል ናቸው፡፡
የፕሮጀክቱ ፕሮግራምና ፈንድ ሞቢላይዜሽን ማኔጀር አቶ ዘገየ ዛግሌ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ መቀመጫውን አዲስ አበባ አድርጎ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የልማት ክንፍ በጋሞና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን አካባቢ የልማት ሥራዎችን የሚሠራ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ አሠራር ውስጥ ለጋሾች፣ ተጠቃሚ ማኅበረሰብ፣ ፈጻሚዎችና የአካባቢ ሁኔታ አለ ያሉት አቶ ዘገየ እነዚህ ሁኔታዎች የሚቀያየሩ በመሆኑ ባለሙያዎች ራሳቸውን በማዘመን ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት አስተባባሪ መ/ርት አስቴር ሰይፉ በበኩላቸው ሥልጠናው ለፕሮጀክቱ ሥራ አስፈጻሚና የቴክኒክ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን ከፕሮጀክት ንድፈ ሃሳብ ጀምሮ እስከ አፈጻጸም ያለውን ሳይንሳዊ ሂደት ለማሳወቅ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው ለደበኞቻቸው የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት